መክብብ 7:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱን በአንዱ ላይ ጨምሬ ወደ ነገሩ ሁሉ ትርጒም እደርስ ዘንድ፥ እነሆ፥ ይህን ነገር አገኘሁ ይላል ሰባኪው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባኪው እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ መርምሬ ያገኘሁት ነገር ይህ ነው፤ “የነገሮችን ብልኀት መርምሮ ለማግኘት፣ አንዱን በአንዱ ላይ በመጨመር፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበበኛው እንዲህ አለ፦ “እነሆ፦ በተከታታይ መርምሬ ያገኘሁት ሌላ ነገር ደግሞ ይህ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ይህን ነገር አገኘሁ ይላል ሰባኪው፥ መደምደሚያን ለማግኘት አንዲቱን በአንዲቱ ጨምሬ ወደ ነገሩ ሁሉ መደምደሚያ እደርስ ዘንድ ብመረምር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱን በአንዱ ላይ ጨምሬ ወደ ነገሩ ሁሉ መደምደሚያ እደርስ ዘንድ፥ እነሆ፥ ይህን ነገር አገኘሁ ይላል ሰባኪው፥ |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
ነፍሴ እስከ ዛሬ ድረስ ትሻታለች፥ ነገር ግን አላገኘሁም፥ ከሺህ ወንዶች አንድ አገኘሁ፥ ከእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ሴት አላገኘሁም።