የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከመስክ መጡ፥ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፥ እንዲህ አይደረግምና እጅግም ተቈጡ።
መክብብ 7:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውቅና እመረምር ዘንድ፥ ጥበብንና የነገሩን ሁሉ ትርጒም እፈልግ ዘንድ፥ ክፋትም አላዋቂነት፥ አላዋቂነትም እብደት እንደሆነ አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጥበብንና የነገሮችን አሠራር ለመመርመርና ለማጥናት፣ የክፋትን መጥፎነት፣ የሞኝነትንም እብደት ለማስተዋል፣ አእምሮዬን መለስሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብንና የነገሮችን ሁናቴ ለመረዳት፥ ለማጥናትና ለመመርመር አሰብኩ፤ ይህም ክፋት ሞኝነት መሆኑን፥ ሞኝነትም እብደት መሆኑን ወደማወቅ አደረሰኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውቅና እመረምር ዘንድ ጥበብንና የነገሩን ሁሉ መደምደሚያ እፈልግ ዘንድ፥ የክፉዎችንም ስንፍናና ዕብደት አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አውቅና እመረምር ዘንድ፥ ጥበብንና የነገሩን ሁሉ መደምደሚያ እፈልግ ዘንድ፥ ኃጢአትም ስንፍና፥ ስንፍናም እብደት እንደ ሆነች አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ። |
የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከመስክ መጡ፥ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፥ እንዲህ አይደረግምና እጅግም ተቈጡ።
እርሷም እንዲህ አለችው፤ “አይሆንም፥ ወንድሜ፥ ተው አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አስነዋሪ ድርጊት አትፈጽም።
እኔም ጥበብን ዕብደትንና አለማወቅን ለመመርመር ወሰንኩ፥ በፊት የተደረገውን መድገም ካልሆነ በቀር፥ ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ያደርጋል?
እኔም በልቤ፦ በአላዋቂ ላይ የሚደርሰው በእኔም ላይ ይደርሳል፤ ለምን እጅግ ጠቢብ ሆንሁ? አልሁ። የዚያን ጊዜም በልቤ፦ ይህ ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።
ተነሣና ሕዝቡን ቀድስ፥ እንዲህም በላቸው፦ ‘እስከ ነገ ተቀደሱ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፦ “እስራኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፤ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።”