መክብብ 12:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባኪው “ከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበበኛው፥ “ከንቱ! ከንቱ! ሁሉ ነገር ከንቱ ነው!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባኪው አለ፥ “ሁሉ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል። |
ደግሞም የሰውን ድካምና የብልሃት ሥራውን ሁሉ ተመለከትሁ፥ በባልንጀራም ዘንድ ቅንዓት እንደሚያስነሣ አየሁ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
ሰው በከንቱ የሕይወቱ ቀናት ቍጥር ና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ለሰው ማን ይነግረዋል?
መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም።