La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መክብብ 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሆነው ነገር ወደፊትም የሚሆነው ነው፥ የተደረገውም ነገር ወደ ፊት የሚደረገው ነው፥ ከፀሐይም በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የነበረው ነገር እንደ ገና ይሆናል፤ የተደረገውም ተመልሶ ይደረጋል፤ ከፀሓይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀድሞ የሆነው ነገር እንደገና ይሆናል፤ አሁንም የሚደረገው ነገር ሁሉ ያው ቀድሞ የተደረገው ነው፤ ስለዚህ በመላው ዓለም አዲስ ተብሎ የሚጠራ ምንም ነገር የለም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሆ​ነው ነገር እርሱ የሚ​ሆን ነው፥ የተ​ደ​ረ​ገ​ውም ነገር እርሱ የሚ​ደ​ረግ ነው፥ ከፀ​ሐ​ይም በታች ከተ​ደ​ረ​ገው ሁሉ አዲስ ነገር የለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ነገር እርሱ የሚደረግ ነው፥ ከፀሐይም በታች አዲስ ነገር የለም።

Ver Capítulo



መክብብ 1:9
10 Referencias Cruzadas  

ማንም፦ እነሆ፥ ይህ ነገር አዲስ ነው ማለት ይችላልን? እርሱ ከእኛ በፊት በነበሩት ዘመናት ተደርጎአል።


እኔም ጥበብን ዕብደትንና አለማወቅን ለመመርመር ወሰንኩ፥ በፊት የተደረገውን መድገም ካልሆነ በቀር፥ ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ያደርጋል?


አሁን ያለው በፊት ነበረ፥ የሚሆነውም በፊት ሆኖ ነበር፥ እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል።


የሆነው ነገር በሙሉ ስሙ አስቀድሞ ተጠርቷል፥ ሰውም ማን እንደሆነ ታወቀ፥ ከእርሱ ከሚበረታው ጋር መፋረድ አይችልም።


ከዚህ ዘመን ይልቅ ያለፈው ዘመን ለምን ተሻለ? ብለህ አትናገር፥ ይህንን ነገር የመትጠይቀው ክጥበብ ተነሥተህ አይደለምና።


እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ ይህን እናንተም አታውቁም? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን እዘረጋለሁ።


አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ታመነቻለሽ? ጌታ በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና ሴት ወንድን ትከብባለች።”


ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይኖራሉ፤ እነርሱም ጥፋትን የሚያስከትሉ ትምህርቶች አስርገው በማስገባት የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፥ በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋትን ያመጣሉ።


አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፤ የፊተኛው ሰማይና የፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደ ፊት የለም።


በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። እኔንም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።