ለሌዋውያንም የምትሰጡአቸው ስድስቱ የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ እነርሱም ነፍሰ ገዳይ እንዲሸሽባቸው የምትሰጡአቸው ናቸው፤ ከእነዚህም ሌላ አርባ ሁለት ከተሞች ትሰጣላችሁ።
ዘዳግም 4:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም ማድረጉ ትናንት ከትናንት በስቲያም ከዚህ ቀድሞ ጠላትነት ሳይኖረው፥ ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ፥ ገዳዩ ይሸሽባቸው ዘንድ፥ ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት እንዲኖር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም የቈየ ጠላትነት ሳይኖር፣ በድንገት ባልንጀራውን የገደለ ማንኛውም ሰው ሸሽቶ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመሄድ ሕይወቱን ማትረፍ ይችል ዘንድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ማድረጉ ቀድሞ ጠላትነት ሳይኖረው ባለማወቅ ማንኛውንም ሰው የገደለ ሕይወቱን ለማትረፍ ወደዚያ ሄዶ ማምለጥ እንዲችል ነው፤ አምልጦም ከእነዚህ ከተማዎች ወደ አንዲቱ ከገባ ሕይወቱን ያድናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትናንት፥ ከትናት በስቲያም ጠላቱ ያልሆነውን ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ ገዳዩ ይማፀንባቸው ዘንድ፥ ከእነዚህም ከተሞች በአንዲቱ ተማፅኖ በሕይወት ይኖር ዘንድ፤ |
ለሌዋውያንም የምትሰጡአቸው ስድስቱ የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ እነርሱም ነፍሰ ገዳይ እንዲሸሽባቸው የምትሰጡአቸው ናቸው፤ ከእነዚህም ሌላ አርባ ሁለት ከተሞች ትሰጣላችሁ።
ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቤጼር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።
ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።