ዘዳግም 4:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ፥ ከእናንተ የበረቱትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊታችሁ እንዲያስወጣ፥ እናንተንም እንዲያስገባ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ይሰጣችሁ ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ከፊትህ በማስወጣት ወደ ምድራቸው አስገብቶህ ለአንተ ርስት አድርጎ ለመስጠት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ማድረጉ ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ከእናንተ የሚበልጡትንና ኀያላን የሆኑትን ሕዝቦች አስወጥቶ ምድራቸውን ለእናንተ ርስት ለማድረግ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግብፅ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆቹን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥ |
አምላካችን ሆይ! በዚህ ምድር የነበሩትን አሕዛብ ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት ያሳደድህ፥ ለወዳጅህም ለአብርሃም ዘር ለዘለዓለም የሰጠሃት አንተ አይደለህምን?
“ጌታ አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከአንተ የበለጡትን እና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን ባስወጣልህ ጊዜ፥
ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደሆነ፥ እርሱም ከነዓናዊውን ኬጢያዊውንም ኤዊያዊውንም ፌርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ከፊታችሁ ፈፅሞ እንደሚያሳድድ በዚህ ታውቃላችሁ።