La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የፌዖሩን ባዓልን የተከተሉትን ሰዎች ሁሉ ጌታ አምላካችሁ ከመካከላችሁ እንዳጠፋ፥ እግዚአብሔር በባዓል ፌዖር ያደረገውን ዐይኖቻችሁ አይተዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር በበኣል ፌጎር ላይ ምን እንዳደረገ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከመካከላችሁ በኣል ፌጎርን የተከተሉትን ሁሉ አጥፍቷቸዋል፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በፔዖር ተራራ ላይ እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ራሳችሁ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ይኸውም በዚያ ተራራ ላይ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት የሚሰግዱትን ሁሉ ደምስሶአል፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብዔ​ል​ፌ​ጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ለ​ውን ሰው ሁሉ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ለይቶ አጥ​ፍ​ቶ​ታ​ልና አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ዔ​ል​ፌ​ጎር ያደ​ረ​ገ​ውን ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብዔልፎጎርን የተከተሉትን ሰዎች ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከመካከላችሁ እንዳጠፋ፥ እግዚአብሔር በብዔልፎጎር ያደረገውን ዓይኖቻችሁ አይተዋል።

Ver Capítulo



ዘዳግም 4:3
9 Referencias Cruzadas  

ለልጆቻቸውም በምድረ በዳ እንዲህ አልኋቸው፦ በአባቶቻችሁ ሥርዓት አትሂዱ ወጋቸውንም አትጠብቁ በጣዖቶቻቸውም አትርከሱ።


እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ እንደ ወይን ዘለላ ሆኖ አገኘሁት፤ አባቶቻችሁንም በወቅቱ መጀመሪያ ላይ እንዳለ እንደ በለስ በኵራት በበለስ ዛፍ ላይ ሆነው አየኋቸው፤ እነርሱ ግን ወደ ባዓል-ፌዖር መጡ፥ ለእፍረትም ነገር ራሳቸውን ለዩ፥ እንደ ወደዱትም ርኩስ ሆኑ፥


ነገር ግን ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ የእስራኤልን ልጆች በቈጠሩአቸው ጊዜ ከነበሩት ከእነዚያ መካከል አንድም ሰው አልነበረም።


እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር ጌታን አታልለው ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ በዚህም ምክንያት በጌታ ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ።


የእናንተ ዐይኖች ግን ጌታ ያደረጋቸውን ሥራዎች ሁሉ አይተዋል።”


እናንተ ግን ጌታ አምላካችሁን የተከተላችሁ ሁላችሁ እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወት ትኖራላችሁ።


በጌታ ማኅበር ላይ መቅሰፍት ያወረደውና እኛ እስከ ዛሬ ድረስ ከእርሱ ያልነጻንበት የፌጎር ኃጢአት ጥቂት ነውን?