ዘዳግም 32:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤ ፍሬያቸው በመርዝ የተሞላ፥ ዘለላቸውም መራራ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይናቸው ከሰዶም ወይን፣ ከገሞራም ዕርሻ ይመጣል፤ የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፣ ዘለላቸውም በምሬት የተሞላ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችን እንደ ሰዶምና ገሞራ የረከሱ ናቸው፤ እነርሱም መራራና መርዘኛ ፍሬ እንደሚሰጥ የወይን ተክል ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ ሐረጋቸውም ከገሞራ ነው፤ ፍሬአቸውም ሐሞት ነው፤ ዘለላቸውም መራራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ 2 ከገሞራም እርሻ ነው፤ 2 ፍሬያቸው ሐሞት ነው፤ 2 ዘለላውም መራራ ነው። |
እኔ የተመረጠች ወይን ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን የተበላሸ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?
በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከጌታ ከእግዚአብሔር የሚመልስ ወንድም ሆነ ሴት ቤተሰብም ሆነ ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ከመካከልህ እንዲህ ያለውን መርዘኛና መራራ የሆነ ፍሬ የሚያበቅል አይገኝባችሁ።