ዘዳግም 24:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህ አስታውስ፤ ስለዚህ ይህን ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርህ አስታውስ፤ ይህን እንድታደርግ ያዘዝሁህ ለዚህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርክ አትርሳ፤ እኔም ይህን ትእዛዝ የሰጠሁህ በዚህ ምክንያት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም በግብፅ ሀገር መጻተኛ እንደ ነበርህ ዐስብ፤ ስለዚህ ይህን ነገር ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም በግብፅ አገር ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ፤ ስለዚህ ይህን ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ። |
ነገር ግን ጌታ ስለ ወደዳችሁ፥ አባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አወጣችሁ።