ዘዳግም 24:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይራ ዛፍህን ፍሬ በምታራግፍበት ጊዜ፣ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሰህ አትሂድ፤ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይራ ዛፍ ፍሬህንም አንድ ጊዜ ከለቀምክ በኋላ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ እንደገና ወደ እርሱ አትመለስ፤ እርሱን ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይራህን ፍሬ በለቀምህ ጊዜ ከቅርንጫፎቹ ላይ አጥርተህ ለመልቀም ዳግመኛ አትመለስ፤ ለመጻተኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመበለትም ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወይራህን ፍሬ ባረገፍህ ጊዜ ከቅርንጫፎቹ ላይ ማርገፉን ለማጣራት አትመለስ፤ ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም ይሁን። |
“የዕርሻህን ሰብል በምታጭድበት ጊዜ፥ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሰህ አትሂድ። ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።