ሐዋርያት ሥራ 4:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈስ ቅዱስም በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ ‘አሕዛብ ለምን አጉረመረሙ? ሕዝቡስ ከንቱን ነገር ለምን አሰቡ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንፈስ ቅዱስም አማካይነት በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤ “ ‘አሕዛብ ለምን በቍጣ ተነሣሡ? ሕዝቡስ ለምን በከንቱ አሤሩ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለህ የተናገርክ አንተ ነህ፤ ‘አሕዛብ ስለምን ተቈጡ? ሕዝቦችስ ስለምን በከንቱ ዶለቱ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ራስህ በአባታችን በባሪያህ በዳዊት አፍ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ ብለህ የተናገርህ፦ አሕዛብ ለምን ተሰበሰቡ? ሕዝቡስ ለምን ከንቱ ነገርን ተናገሩ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንፈስ ቅዱስም በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ፦ አሕዛብ ለምን አጕረመረሙ? ሕዝቡስ ከንቱን ነገር ለምን አሰቡ? |
“ወንድሞች ሆይ! ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤