ሐዋርያት ሥራ 26:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አግሪጳም ፈስጦስን “ይህ ሰው እኮ ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ይፈታ ዘንድ ይቻል ነበር፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አግሪጳም ፊስጦስን፣ “ይህ ሰው ወደ ቄሳር ይግባኝ ባይል ኖሮ መልቀቅ ይቻል ነበር” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አግሪጳም ፊስጦስን “ይህ ሰው ወደ ሮሙ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ባይል ኖሮ በነጻ በተለቀቀ ነበር” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አግሪጳም ፊስጦስን፥ “ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ኖሮ ይህ ሰው ይፈታ ዘንድ በተገባ ነበር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አግሪጳም ፈስጦስን፦ ይህ ሰው እኮ ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ይፈታ ዘንድ ይቻል ነበር” አለው። |