ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።
ሐዋርያት ሥራ 20:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይልቁንም “ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም፤” ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሁሉም በላይ ልባቸውን የነካው፣ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቱን እንደማያዩ የተናገራቸው ቃል ነበር። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቁንም በጣም ያዘኑት፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም” ብሎአቸው ስለ ነበር ነው፤ እስከ መርከብ ድረስም ሸኙት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይልቁንም “ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩትም” ስለ አላቸው እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይልቁንም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት። |
ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።
በቂሣርያም ከነበሩ ደቀ መዛሙርት አንዳንዶች ደግሞ ከእኛ ጋር መጡ፤ እነርሱም ወደምናድርበት ወደ ቀደመው ደቀመዝሙር ወደ ቆጵሮሱ ምናሶን ወደሚሉት ቤት መሩን።
ጊዜውንም በፈጸምን ጊዜ ወጥተን ሄድን፤ ሁላቸውም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን፤
ስለ እርሱም ወደ ጌታዬ የምጽፈው እርግጥ ነገር የለኝም፤ ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈውን ነገር አገኝ ዘንድ በፊታችሁ ይልቁንም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ!በፊትህ አመጣሁት፤