እኛ ግን ጳውሎስን ከዚያ እንቀበለው ዘንድ ስላለን ወደ መርከብ ቀድመን ሄድንና ወደ አሶን ተነሣን፤ እርሱ በመሬት ይሄድ ዘንድ ስላሰበ እንደዚህ አዞ ነበርና።
ሐዋርያት ሥራ 20:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሶንም ባገኘን ጊዜ ተቀብለነው ወደ ሚጢሊኒ መጣን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአሶን ከተገናኘንም በኋላ፣ ተቀብለነው ዐብረን በመርከብ ወደ ሚጢሊኒ ሄድን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ ጋር በአሶስ በተገናኘን ጊዜ በመርከብ አሳፍረነው ወደ ሚጢሊኒ አብረን ሄድን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሶስም ደረስን፤ በመርከብም ይዘነው ወደ ሚጢሊኒ ሄድን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሶንም ባገኘን ጊዜ ተቀብለነው ወደ ሚጢሊኒ መጣን፤ |
እኛ ግን ጳውሎስን ከዚያ እንቀበለው ዘንድ ስላለን ወደ መርከብ ቀድመን ሄድንና ወደ አሶን ተነሣን፤ እርሱ በመሬት ይሄድ ዘንድ ስላሰበ እንደዚህ አዞ ነበርና።
በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፤ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን።