ሐዋርያት ሥራ 17:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም በምኵራብ ከአይሁድና እግዚአብሔርን ከሚያመልኩ ሰዎች ጋር በየቀኑም በገበያ ከሚያገኛቸው ጋር ይነጋገር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በምኵራብ ሆኖ ከአይሁድና እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ግሪኮች ጋራ፣ ደግሞም በገበያ ስፍራ ዕለት ዕለት ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋራ ይነጋገር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በምኲራብ ከአይሁድና እግዚአብሔርንም ከሚያመልኩት ሰዎች ጋር በአደባባይም በየቀኑ ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይከራከር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም በምኵራብ አይሁድንና እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ ሁልጊዜም በገበያ የሚያገኛቸውን ሁሉ ይከራከራቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም በምኵራብ ከአይሁድና እግዚአብሔርን ከሚያመልኩ ሰዎች ጋር በየቀኑም በገበያ ከሚያገኛቸው ጋር ይነጋገር ነበር። |
ስለዚህ በጌታ ቁጣ ተሞልቻለሁ፤ ከመታገሥ ደክሜአለሁ፤ “በጎዳና ባሉ ሕፃናት ላይ በጉልማሶችም ጉባዔ ላይ በአንድነት አፍስሰው፤ ደግሞም ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም በእድሜአቸው ከገፉት ጋር ይያዛሉና።
እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ።
ጉባኤውም ከተፈታ በኋላ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ገብተው ከሚያመልኩ ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሉአቸው፤ እነርሱም ሲነግሩአቸው በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ አስረዱአቸው።
አይሁድ ግን የሚያመልኩትን የከበሩትንም ሴቶችና የከተማውን መኳንንት አወኩ፤ በጳውሎስና በበርናባስም ላይ ስደትን አስነሥተው ከአገራቸው አወጡአቸው።
ሰዎች እንዲህ ይሆናሉና፤ ራሳቸውን የሚወዱ፥ ገንዘብን ወዳጆች፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥