በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በደላቸውን ይቅር በል፤ እርዳቸው፤ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን ሐሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው።
ሐዋርያት ሥራ 15:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልብን የሚያውቅ አምላክ ለእኛ እንደ ሰጠን ሁሉ፣ ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት የተቀበላቸው መሆኑን መሰከረላቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰውን ልብ የሚያውቅ አምላክ፥ መንፈስ ቅዱስን ለእኛ እንደ ሰጠው ዐይነት ለእነርሱም በመስጠት መሰከረላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብን የሚያውቅ እግዚአብሔርም ለእኛ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤ |
በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በደላቸውን ይቅር በል፤ እርዳቸው፤ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን ሐሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው።
“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።
አምላኬ ሆይ! ልብን እንደምትመረምር፥ ቅንነትንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱና ደስ ተሰኝቶ እንዳቀረበልህ አይቻለሁ።
ነገር ግን ኩላሊትንና ልብን የምትመረምር በቅንም የምትፈርድ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ሙግቴን ገልጬልሃለሁና በእነርሱ ላይ የሚሆነውን በቀልህን ልይ።
ለሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ለሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም “በጎቼን አሰማራ።
ሲጸልዩም “የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ! ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው፤” አሉ።
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ “እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውሃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው?” አለ።
ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።”
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
ጌታ ግን ሳሙኤልን፥ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። ጌታ የሚያየው፥ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ ጌታ ግን ልብን ያያል” አለው።