በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ “እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውሃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው?” አለ።
ሐዋርያት ሥራ 10:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስ ይህን እየተናገረ ሳለ፣ ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጴጥሮስ ይህን በሚናገርበት ጊዜ ቃሉን በሰሙት ሰዎች ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስም ይህን ነገር ሲነግራቸው ይህን ትምህርት በሰሙት ሰዎች ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። |
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ “እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውሃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው?” አለ።