ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፥ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፥ በምድርም መካከል ይብዙ።”
2 ጢሞቴዎስ 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስደቴንም፥ መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የደረሰብኝን ነገርና የታገሥሁትን ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከሁሉም አዳነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስደቴንና መከራዬን፣ በአንጾኪያና በኢቆንዮን፣ በልስጥራንም የደረሰብኝን ሁሉ፣ የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከእነዚህ ሁሉ አዳነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ስደቴንና መከራዬን ታውቃለህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የደረሰብኝን ነገርና በትዕግሥት የተቀበልኩትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከሁሉም አዳነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ። |
ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፥ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፥ በምድርም መካከል ይብዙ።”
በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰምጡህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
ብዙ ጥልም በሆነ ጊዜ የሻለቃው ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ጭፍሮቹ ወርደው ከመካከላቸው እንዲነጥቁት ወደ ሰፈሩም እንዲያገቡት አዘዘ።
የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዐይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።’
ከእግዚአብሔርም ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ ይሆን ዘንድ ያለውን፥ ክርስቶስ መከራን እንዲቀበል በሙታንም ትንሣኤ ለሕዝብና ለአሕዛብ ብርሃንን በመጀመሪያ ሊሰብክ እንዳለው፥ ከተናገሩት በቀር አንድ ስንኳ የተናገርሁት የለም።”
እንግዲህ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸው፥ እንዲሁም በደለኞችን እንዴት በቅጣት ስር ለፍርድ ቀንም ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።