2 ሳሙኤል 18:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰው ይህን አይቶ ለኢዮአብ፥ “እነሆ፤ አቤሴሎም በባሉጥ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ይህን አይቶ ለኢዮአብ፣ “እነሆ፤ አቤሴሎም በባሉጥ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዳዊት ወታደሮችም አንዱ ይህን አይቶ ለኢዮአብ “ጌታዬ፤ አቤሴሎምን በወርካ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት!” ብሎ ነገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ሰውም አይቶ፥ “እነሆ፥ አቤሴሎም በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁ” ብሎ ለኢዮአብ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰውም አይቶ፦ እነሆ፥ አቤሴሎም በትልቅ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁ ብሎ ለኢዮአብ ነገረው። |
ኢዮአብም ይህን የነገረውን ሰው፥ “ምን አልህ! ካየኸው ታዲያ ለምንድን ነው ያኔውኑ መተህ ምድር ላይ ያልጣልኸው? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ፥ ዐሥር ብርና ዝናር እሸልምህ ነበር” አለው።
በዚህ ጊዜ አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ጋር ድንገት ተገናኘ፤ አቤሴሎም በበቅሎ ተቀምጦ ይሄድ ስለ ነበር፥ በቅሎዋ ጥቅጥቅ ያለ ቅርንጫፍ ባለው ትልቅ ባሉጥ ሥር በምታልፍበት ጊዜ፥ የአቤሴሎም ራስ በባሉጡ ቅርንጫፍ ተያዘ፤ የተቀመጠበትም በቅሎ በሥሩ ስታልፍ፥ እርሱ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠልጥሎ ቀረ።
ከእርሱ ዘሮች ሰባት ወንዶች ልጆች ይሰጠን፤ እኛም ከጌታ በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ በጌታ ፊት እንስቀላቸው” ብለው መለሱለት። ስለዚህ ንጉሡ፥ “እሺ! እሰጣችኋለሁ” አለ።