La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 16:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን፤ “ይህ የሞተ ውሻ፥ ንጉሥ ጌታዬን እንዴት ይራገማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን፣ “ይህ የሞተ ውሻ፣ ንጉሥ ጌታዬን እንዴት ይራገማል? ልሻገርና ራሱን ልቍረጠው” አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ጊዜ የጸሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን እንዴት ይራገማል? እኔ ሄጄ ራሱን ልቊረጠው!” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢ​ሳም ንጉ​ሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ስለ​ምን ይረ​ግ​ማል? ልሻ​ገ​ርና ራሱን ልቍ​ረ​ጠው፤”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጽሩያም ልጅ አቢሳ ንጉሡን፦ ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን ስለምን ይረግማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው አለው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 16:9
13 Referencias Cruzadas  

እኔ አገልጋይህ ኃጢአት መሥራቴን አውቃለሁና፤ እነሆ፥ ዛሬ ግን ጌታዬ ንጉሡን ለመቀበል ከዮሴፍ ቤት ሁሉ የመጀመሪያ ሆኜ መጥቻለሁ።”


ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ፥ “ሺምዒ በጌታ የተቀባውን የረገመ ስለሆነ፥ መሞት አይገባውምን?” አለ።


አበኔር ገባዖን ላይ በተደረገው ጦርነት የኢዮአብንና የአቢሳን ወንድም አሣሄልን ገድሎት ስለ ነበር፥ እነርሱም አበኔርን ገደሉት።


ይህ የአበኔር ንግግር እጅግ ያስቆጣው ኢያቡስቴ እንዲህ አለ፤ “እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት፥ ለወንድሞቹና ለዘመዶቹ፥ ታማኝነቴን ሳላጎድል ይሄው አለሁ፤ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁም፥ ዛሬ ግን አንተ በዚህች ሴት ትከሰኛለህን? በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝ?


መፊቦሼት ለጥ ብሎ እጅ ነሣና፥ “እንደ ሞተ ውሻ ለምቆጠር ለእኔ ይህን ያህል የምታደርግልኝ አገልጋይህ ኧረ ማን ነኝ?” አለ።


ከሙላትህና ከጭማቂህ ለማቅረብ አትዘግይ፤ የልጆችህንም በኩር ትሰጠኛለህ።


ደቀመዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ “ጌታ ሆይ! ከሰማይ እሳት ወርዶ እንዲበላቸው እንድናዝዝ ትወዳለህን?” አሉት።


ጳውሎስም “ወንድሞች ሆይ! ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው፤ ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር፤’ ተብሎ ተጽፎአልና፤” አላቸው።


ሰውን ሁሉ አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


ጥንት፥ ‘ክፋት ክፋትን ይወልዳል’ እንደተባለ፤ አሁንም እጄ በአንተ ላይ አትሆንም።