ስለዚህም ዳዊትና ሰዎቹ መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሺምዒ በተራራው አጠገብ በእርሱ ትይዩ እየሄደ ይራገም ድንጋይም ይወረውር፥ ዐፈርም ይበትን ነበር።
2 ሳሙኤል 16:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጣም ደክሞአቸው ስለ ነበር በዚያ ዐረፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ ለመሄድ ወዳሰቡበት ስፍራ ደረሱ፤ በጣም ደክሟቸው ስለ ነበር በዚያ ዐረፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ በጣም ደክሞአቸው ስለ ነበር በዚያ ዕረፍት አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ሁሉ ደረሱ፤ ደክመውም ነበር፤ በዚያም ዐረፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ሁሉ ደክመው ነበር፥ በዚያም ዐረፉ። |
ስለዚህም ዳዊትና ሰዎቹ መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሺምዒ በተራራው አጠገብ በእርሱ ትይዩ እየሄደ ይራገም ድንጋይም ይወረውር፥ ዐፈርም ይበትን ነበር።
ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም ሲደርስ፥ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ወጣ፤ ስሙ ሺምዒ ሲሆን የጌራ ልጅ ነው፤ እየተራገመም ወደ እርሱ ይመጣ ነበር።
ማር፥ እርጎ፥ በጎችና የላም አይብ እንዲበሉ ለዳዊትና ለሕዝቡ አመጡላቸው፤ ይህን ያደረጉትም፥ “ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፤ ደክሞአል፤ ተጠምቶአል” ብለው ነው።