2 ሳሙኤል 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልእክተኛም መጥቶ፥ “የእስራኤል ሰዎች ልብ ከአቤሴሎም ጋር ሆኖአል” ብሎ ለዳዊት ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልእክተኛም መጥቶ፣ “የእስራኤል ሰዎች ልብ ከአቤሴሎም ጋራ ሆኗል” ብሎ ለዳዊት ነገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ መልእክተኛ ዳዊትን “እስራኤላውያን ታማኝነታቸውን ለአቤሴሎም በመግለጥ ላይ ናቸው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሰዎች ልብ ወደ አቤሴሎም ተመልሶአል የሚል መልእክተኛ ወደ ዳዊት ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዳዊትም፦ የእስራኤል ሰዎች ልብ ከአቤሴሎም ጋር ሆኖአል የሚል ወሬኛ መጣለት። |
ከፊቱ ይሄዱ የነበሩትና ይከተሉት የነበሩት ሕዝብ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
የእናቱ ዘመዶች ስለ እርሱ ሆነው እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለሴኬም ነዋሪዎች በሙሉ ነገሩ፤ “እርሱማ ወንድማችን አይደል” ብለዋልና፥ አቤሜሌክንም ለመከተል ልባቸው ወደሱ አዘነበለ።