2 ሳሙኤል 14:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አቤሴሎም ወደ ንጉሡ እንዲሄድለት ኢዮአብን አስጠራው፤ ኢዮአብ ግን ወደ እርሱ አልመጣም፤ ለሁለተኛ ጊዜም ላከበት፤ ኢዮአብ ግን አሁንም ሳይመጣ ቀረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አቤሴሎም ወደ ንጉሡ እንዲሄድለት ኢዮአብን አስጠራው፤ ኢዮአብ ግን ወደ እርሱ መምጣት አልፈለገም፤ ለሁለተኛ ጊዜም ላከበት፤ ኢዮአብ አሁንም መምጣት አልፈለገም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን በኋላ ወደ ንጉሡ ቀርቦ እንዲጠይቅለት ኢዮአብን አስጠራ፤ ኢዮአብ ግን መምጣት አልፈቀደም፤ አቤሴሎም እንደገና ኢዮአብ እንዲመጣለት መልእክት ላከ፤ ኢዮአብ ግን አሁንም ሳይመጣ ቀረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ ይልከው ዘንድ ወደ ኢዮአብ ላከ፤ ወደ እርሱም ሊመጣ አልወደደም፤ ሁለተኛም ላከበት፤ ሊመጣ ግን አልወደደም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ ይልከው ዘንድ ወደ ኢዮአብ ላከ፥ ወደ እርሱም ሊመጣ አልወደደም፥ ሁለተኛም ላከበት፥ ሊመጣ ግን አልወደደም። |