2 ሳሙኤል 13:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ትዕማር ወንድሟ አምኖን ወደ ተኛበት ቤት ሄደች፤ ጥቂት ሊጥ ወስዳ ካቦካች በኋላ እያየ ጋገረችው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ትዕማር ወንድሟ አምኖን ወደ ተኛበት ቤት ሄደች፤ ጥቂት ሊጥ ወስዳ ካቦካች በኋላ እያየ አዘጋጅታ ጋገረችው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት በሄደች ጊዜ አልጋ ላይ ተኝቶ አገኘችው፤ ጥቂት ሊጥ ወስዳ በማቅጠንም አምኖን እያያት እንጀራ ጋገረች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዕማርም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፤ ተኝቶም ነበር፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰች፤ በፊቱም እንጎቻ አደረገች፤ ጋገረችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዕማርም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፥ ተኝቶም ነበር፥ ዱቄትም ወስዳ ለወሰች፥ እያየም እንጎቻ አደረገች፥ ጋገረችም። |
ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ እንጀራውን አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መብላት አልፈለገም። አምኖንም፥ “ሰውን ሁሉ ከዚህ አስወጡልኝ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ትቶት ወጣ።