የወይን ጠጅ በደረቁ ቢጠጣ እንደሚጐዳ ሁሉ ውሃም ለብቻው አይወሰድም፤ ነገር ግን የወይን ጠጅ ከውሃ ጋር በተቀላቀለ ጊዜ ጣፋጭና የደስታን ስሜት የሚፈጥር ነው። እንደዚሁ ሁሉ የተለያዩ አጋጣሚዎችን በተገቢው መልክ የማቅረብ ችሎታ መጽሐፉን ለሚያነቡ ሁሉ የግንዛቤን ደስታ ይሰጣል። እኔም ጽሑፌን በዚህ አበቃለሁ።