ከኢየሩሳሌም ሽማግሌዎች አንዱ ራዝያስ የተባለ ሰው በኒቃኖር ፊት ተከሰሰ፤ ይህ ሰው የሀገሩን ሕዝብ የሚወድ እጅግ ጥሩ ስም ያለው፥ ሰለ ፍቅሩ የአይሁዳውያን አባት ይባል የነበረ ጐምቱ ነው።