2 ነገሥት 4:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዩ ግን “ይህ ለመቶ ሰው የሚበቃ ይመስልሃልን?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “እንዲበሉ አቅርብላቸው፤ በልተው መጥገብ ብቻ ሳይሆን እንደሚተርፋቸውም እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዩም፣ “ይህን እንዴት አድርጌ ለመቶ ሰው አቀርባለሁ?” ሲል ጠየቀ። ኤልሳዕ ግን፣ “እንዲበሉት ለሰዎቹ ስጣቸው፤ እግዚአብሔር፣ ‘በልተው ይተርፋቸዋል’ ይላልና” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዩ ግን “ይህ ለመቶ ሰው የሚበቃ ይመስልሃልን?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “እንዲበሉ አቅርብላቸው፤ በልተው መጥገብ ብቻ ሳይሆን እንደሚተርፋቸውም እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌውም፥ “ይህን እንዴት አድርጌ ለመቶ ሰው አቀርባለሁ?” አለ። እርሱም፥ “ይበላሉ፥ ያተርፋሉም ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮአልና ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌውም “ይህን እንዴት አድርጌ ለመቶ ሰው እሰጣለሁ?” አለ። እርሱም “‘ይበላሉ ያተርፋሉም፤’ ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮአልና ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው፤” አለ። |
እርሱ ግን፦ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። እነርሱም፦ “ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን በቀር ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ የሚበልጥ የለንም፤” አሉት፤