2 ነገሥት 4:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከልጁ ጋር ብቻውን ሆኖ፥ ክፍሉንም ዘግቶ፥ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ውስጥም ገባ፤ ከዚያም በሩን በራሱና በልጁ ላይ ዘግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከልጁ ጋር ብቻውን ሆኖ፥ ክፍሉንም ዘግቶ፥ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም ወደ ቤት ገብቶ በሩን በሁለቱ ላይ ዘጋ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገብቶም በሩን ከሁለቱ በኋላ ዘጋ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ። |
ከዚህም በኋላ አንቺና ልጆችሽ ወደ ቤት ገብታችሁ መዝጊያውን ዝጉ፤ የማሰሮውንም ዘይት ወደ ማድጋዎቹ ማንቆርቆር ጀምሩ፤ እያንዳንዱ ማድጋ በሚሞላበት ጊዜ ለብቻው በማግለል አኑሩት።”
ንዕማን ግን ተቆጥቶ ወደ አገሩ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም እያለ ያጉረመርም ነበር፤ “እኔ እኮ ነቢዩ መጥቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የቆዳው በሽታ ባረፈበት ገላዬ ላይ እጆቹን በመወዝወዝ ይፈውሰኛል ብዬ አስቤ ነበር!
ወደ ከተማይቱም እንደ ገቡ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችሉ ዐይኖቻቸውን ግለጥላቸው!” ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ዐይኖቻቸውን በከፈተላቸው ጊዜ በሰማርያ ውስጥ መሆናቸውን ተረዱ።
ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፤ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ “ጣቢታ ሆይ! ተነሺ፤” አላት። እርሷም ዐይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።