La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 22:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወዲያውኑ ለካህኑ ለሒልቂያ፥ የሳፋን ልጅ ለሆነው ለአሒቃም፥ የሚካያ ልጅ ለሆነው ለዐክቦር፥ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ለሆነው ለሳፋንና የንጉሡ የቅርብ አገልጋይ ለሆነው ለዓሳያ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጠ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ንጉሡ ካህኑን ኬልቅያስን፣ የሳፋን ልጅ አኪቃምን፣ የሚክያስን ልጅ ዓክቦርን፣ ጸሓፊውን ሳፋንንና የንጉሡን የቅርብ አገልጋይ ዓሳያን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወዲያውኑ ለካህኑ ለሒልቂያ፥ የሳፋን ልጅ ለሆነው ለአሒቃም፥ የሚካያ ልጅ ለሆነው ለዐክቦር፥ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ለሆነው ለሳፋንና የንጉሡ የቅርብ አገልጋይ ለሆነው ለዓሳያ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጠ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ካህ​ኑን ኬል​ቅ​ያ​ስን፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ አኪ​ቃ​ምን፥ የሚ​ክ​ዩ​ንም ልጅ ዓክ​ቦ​ርን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳፋ​ንን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ብላ​ቴና ዓስ​ያን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ካህኑን ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ ዓክቦርን፥ ጸሐፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዓሳያን

Ver Capítulo



2 ነገሥት 22:12
9 Referencias Cruzadas  

ሒልቂያ፥ አሒቃም፥ ዐክቦር፥ ሳፋንና ዐሣያ በኢየሩሳሌም አዲስ በተሠራው ሰፈር የምትኖረውን ሑልዳ ተብላ የምትጠራውን ነቢይት ለመጠየቅ ሄዱ፤ የሐርሐስ የልጅ ልጅ የቲቅዋ ልጅ የሆነው ባሏ ሻሉም የቤተ መቅደስ አልባሳት ኃላፊ ነበር፤ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ለነቢይቱ አስረዱአት።


ከዚያም በኋላ ጸሐፊው ሳፋን ወደ ንጉሡ ተመልሶ ሄደና “አገልጋዮችህ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበረውን ገንዘብ ተቀብለው ለእድሳቱ ሥራ ኃላፊዎች ለሆኑት ሰዎች አስረክበዋል” ሲል አስረዳ፤


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የሳፋን የልጅ ልጅ የአሒቃም ልጅ ገዳልያን ወደ ባቢሎን ተማርከው ሳይወሰዱ ለቀሩት ሰዎች ሁሉ ኃላፊ ይሆን ዘንድ የይሁዳ ገዢ አድርጎ ሾመው።


ንጉሡም ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንን ከእርሱም ጋር ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፤


ነገር ግን በሕዝቡ እጅ እንዳይሰጥና እንዳይገድሉት የሳፋን ልጅ የአኪቃም እጅ ከኤርምያስ ጋር ነበረች።


ልከው ኤርምያስን ከእስር ቤት አደባባይ አወጡት፤ ወደ ቤቱም እንዲወስደው ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ እርሱም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።