2 ቆሮንቶስ 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ከእርሱ ጋር ፍቅራችሁን መልሳችሁ እንድታጸኑ እለምናችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አሁንም የምትወድዱት መሆናችሁን እንድትገልጹለት እለምናችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እርሱን የምትወዱት መሆናችሁን እንደገና እንድታረጋግጡለት እለምናችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ከእርሱ ጋር ፍቅርን እንድታጸኑ እማልዳችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ከእርሱ ጋር ፍቅርን እንድታጸኑ እለምናችኋለሁ፤ |
ወንድሞች ሆይ! እናንተ ለነጻነት ተጠርታችኋል፤ ነጻነታችሁ ለሥጋ ብቻ ምክንያት አይስጥ፤ ነገር ግን በፍቅር አንዳችሁ ለሌላችሁ ባርያዎች ሁኑ።