2 ቆሮንቶስ 13:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም የምለው ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንደሆነ ማስረጃ በመፈለጋችሁ ነው፤ ክርስቶስ ስለ እናንተ አይደክምም፤ ነገር ግን በመካከላችሁ ኀያል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሚሆነው ክርስቶስ በእኔ ዐድሮ እንደሚናገር ማስረጃ በመፈለጋችሁ ነው። እርሱም በመካከላችሁ ብርቱ እንጂ ደካማ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በእኔ ዐድሮ የሚናገረው ክርስቶስ መሆኑን ለማረጋገጥ ትፈልጋላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ የሚታየውም የእርሱ ኀይል ነው እንጂ ድካሙ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንደሚናገር ማስረጃ ትሻላችሁና፤ እርሱም ሁሉ የሚቻለው ነው እንጂ፥ በእናንተ ዘንድ የሚሳነው የለም። |