2 ዜና መዋዕል 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም እንዲህ አለ፦ “ጌታ፦ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እኖራለሁ ብሏል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ጥቅጥቅ ባለ ደመና ውስጥ እንደሚኖር ተናግሯል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ ‘በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እኖራለሁ’ ብለሃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም ሰሎሞን፥ “እግዚአብሔር፦ በጨለማ ውስጥ እኖራለሁ ብሎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም “እግዚአብሔር ‘በጨለማ ውስጥ እኖራለሁ፤’ ብሎአል፤ |
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና፥ እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደተቀደሰው ስፍራ፥ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።
ጌታ ለቁጣ የዘገየ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፤ ጌታ መንገዱ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።
እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፥ እስከ ሰማይም ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፥ ጨለማም ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ።