2 ዜና መዋዕል 36:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ ሦስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአካዝ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ሦስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ወር ገዛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአሐዝ በይሁዳ ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ ሦስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ ሦስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። 2 ‘ሀ’ የእናቱም ስም ከሎቤና የኤርምያስ ልጅ አሚጣል ነበረች። 2 ‘ለ’ አባቶቹ እንደ ሠሩት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራን ሠራ። በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ በኤማት ምድር በዴብላታ ፈርዖን ኒካዑ ማርኮ አሰረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ ሦስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። |