2 ዜና መዋዕል 35:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ንጉሡም እንደ ኢዮስያስ ትእዛዝ በጌታ መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ፋሲካውንም እንዲያከብሩ የጌታ አገልግሎት ሁሉ በዚያ ቀን ተዘጋጀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ዐይነት የፋሲካን በዓል በማክበርና የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ በማቅረብ የእግዚአብሔር አገልግሎት ሁሉ ንጉሥ ኢዮስያስ ባዘዘው መሠረት በዚያ ቀን ተከናወነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ለእግዚአብሔር የሚቀርበው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት፥ የፋሲካ በዓል አከባበርና የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ የማቅረቡ ሥራ ሁሉ ንጉሥ ኢዮስያስ ባዘዘው መሠረት በዚያ ቀን ተከናወነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ንጉሡም እንደ ኢዮስያስ ትእዛዝ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፥ ፋሲካውንም ያደርጉ ዘንድ፥ የእግዚአብሔር አገልግሎት ሁሉ በዚያ ቀን ተዘጋጀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ንጉሡም እንደ ኢዮስያስ ትእዛዝ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፥ ፋሲካውንም ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር አገልግሎት ሁሉ በዚያ ቀን ተዘጋጀ። |
የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍም እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ የደጁም ጠባቂዎች በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው እንዲርቁ አያስፈልጋቸውም ነበር።