2 ዜና መዋዕል 33:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዎቹም አሤሩበት፥ በቤቱም ውስጥ ሳለ ገደሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሞንም ሹማምት በርሱ ላይ አሢረው በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ገደሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሞን ባለሟሎች የሆኑት ባለሥልጣኖች በእርሱ ላይ በማሤር በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ገደሉት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተንም እማልዳለሁ፤ እለምንህማለሁ፤ ይቅር በለኝ፤ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ ለኀጢአቴም አሳልፈህ አትስጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎቹም ተማምለው በቤቱ ገደሉት። |
አካዝያስንም ፈልገው፥ በሰማርያም ተሸሽጎ ሳለ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት እንዲህም ብለው ቀበሩት፦ “በፍጹም ልብ ጌታን የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው።” ከአካዝያስም ቤት ማንም መንግሥቱን ለመግዛት የሚችል አልነበረም።
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ ጭከናው በወደቁት ላይ ነው፤ በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ ትቆረጣለህ።