ይሁዳንም እንዲህ አለ፦ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፥ ቅጥርና ግንብ፥ መዝጊያና መቀርቀሪያ እናድርግባቸው፤ አምላካችንን ጌታን ስለ ፈለግነው ምድሪቱ አሁንም ድረስ የኛው ነች፤ እኛ ፈልገነዋል፥ እርሱም በዙሪያችን ዕረፍት ሰጥቶናል።” እነርሱም ሠሩ ተከናወነላቸውም።
2 ዜና መዋዕል 27:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተራራማውም በይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን ሠራ፥ በዱር ስፍራዎችም አምባዎችንና ግንቦችን ሠራ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሁዳ ኰረብቶች ላይ ከተሞችን፣ ደን በለበሱ ስፍራዎችም ምሽጎችንና ማማዎችን ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በይሁዳ ተራራማ ስፍራዎች ላይ ከተሞችን፥ ደን በበዛባቸው ስፍራዎችም ላይ ምሽጎችንና ቅጽሮችን ሠርቶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተራራማውም በይሁዳ ሀገር ላይ ከተሞችን ሠራ፤ በዱር ስፍራዎችም አምባዎችንና ግንቦችን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተራራማውም በይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን ሠራ፤ በዱር ስፍራዎችም አምባዎችንና ግንቦችን ሠራ። |
ይሁዳንም እንዲህ አለ፦ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፥ ቅጥርና ግንብ፥ መዝጊያና መቀርቀሪያ እናድርግባቸው፤ አምላካችንን ጌታን ስለ ፈለግነው ምድሪቱ አሁንም ድረስ የኛው ነች፤ እኛ ፈልገነዋል፥ እርሱም በዙሪያችን ዕረፍት ሰጥቶናል።” እነርሱም ሠሩ ተከናወነላቸውም።
ከአሞንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ አሸነፋአቸውም። በዚያም ዓመት የአሞን ልጆች መቶ መክሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። እንዲሁም ደግሞ የአሞን ልጆች በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ተመሳሳ መጠን ያለውን ግብር ገበሩለት።