2 ዜና መዋዕል 20:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮሣፍጥም በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ መንገሥ በጀመረ ጊዜም የሠላሳ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሀያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮሣፍጥ በይሁዳ ነገሠ። መንገሥ በጀመረ ጊዜም ዕድሜው ሠላሳ ዐምስት ዓመት ሲሆን፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ሃያ ዐምስት ዓመት ገዛ። እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮሣፍጥ የይሁዳ ንጉሥ የሆነው በሠላሳ አምስት ዓመቱ ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኻያ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱ ዐዙባ ተብላ የምትጠራ የሺልሒ ልጅ ነበረች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮሣፍጥም በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ መንገሥ በጀመረ ጊዜም የሠላሳ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሳሊ ልጅ አዙባ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮሣፍጥም በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ መንገሥ በጀመረ ጊዜም የሠላሳ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሀያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች። |