2 ዜና መዋዕል 16:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባኦስም በሰማ ጊዜ ራማን መሥራት ተወ፥ ሥራውንም አቋረጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባኦስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ራማን መገንባቱን አቆመ፤ ሥራውንም አቋረጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ባዕሻ ይህን በሰማ ጊዜ ራማን ለመመሸግ የጀመረውን ሥራ ተወ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባኦስም በሰማ ጊዜ ራማን መሥራት ተወ፤ ሥራውንም አቋረጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባኦስም በሰማ ጊዜ ራማን መሥራት ተወ፤ ሥራውንም አቍረጠ። |
ወልደ አዴር ንጉሡን አሳን እሺ አለው፥ የሠራዊቱንም የጦር አዛዦች በእስራኤል ከተሞች ላይ ላከ፤ እነርሱም ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልማይምንና ለንፍታሌም እንደ ግምጃ ቤት የሚያገለግሉትን ከተሞች ሁሉ ያዙ።
ንጉሡም አሳ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ እነርሱም ባኦስ ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋይና እንጨት ወሰዱ፥ እርሱም ጌባንና ምጽጳን ሠራበት።