ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፥ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ወጣቶቻችሁም ራእይ ያያሉ፥
1 ጢሞቴዎስ 6:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቋቸው፤ ይልቁንስ ከበፊት ይልቅ ያገልግሏቸው ምክንያቱም በመልካም ሥራቸው የሚጠቀሙት አማኞችና ወዳጆቻቸው ናቸውና። እነዚህን ነገርች አስተምርና ምከር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያምኑ ጌቶች ያሏቸውም፣ ወንድሞች ስለ ሆኑ የሚገባቸውን ክብር አይንፈጓቸው፤ ይልቁንም በአገልግሎታቸው የሚጠቀሙ አማኞችና ወዳጆቻቸው ስለ ሆኑ የበለጠ ሊያገለግሏቸው ይገባል። እነዚህን ነገሮች አስተምር፤ ምከርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌቶቻቸው አማኞች የሆኑ አገልጋዮች በጌታ ኢየሱስ ወንድሞቻቸው ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ይልቅስ ከአገልግሎታቸው ጥቅም የሚያገኙ ጌቶቻቸው አማኞችና የተወደዱ ወንድሞቻቸው ስለ ሆኑ ከበፊት ይበልጥ ያገልግሉአቸው። አንተም ማስተማርና መምከር የሚገባህ ይህን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፥ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ። |
ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፥ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ወጣቶቻችሁም ራእይ ያያሉ፥
በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ ጌታም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችሁታል፤ በጌታም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?”
ንጉሡም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።’
“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”
ነገር ግን ከቅርንጫፎቹ አንዳንዱ ቢሰበሩ አንተም የበረሃ ወይራ የሆንህ በመካከላቸው ገብተህ ከእነርሱ ጋር የወይራ ዘይት ከሚወጣው ሥር ተካፋይ ከሆንህ፥
ይህ የሆነው፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ ነው።
ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ አድጎአልና፥ የእናንተም የእያንዳንዳችሁ ሁሉ ፍቅር ለእርስ በርሳችሁ በዝቶአልና፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግዴታ አለብን፤
ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲተጉ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤
እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር አብሬ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ የሆንኩ፥ የክርስቶስም መከራ ምስክር የሆንኩ፥ እንዲሁም ወደ ፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን፥ በመካከላችሁ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ።
ይልቁንም በርኩስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን፥ ጌትነትንም የሚንቁትን፤ ደፋሮችና እምቢተኞች ስለ ሆኑ ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይፈሩም፤