1 ጢሞቴዎስ 5:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ካልተደገፈ በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ካልተደገፈ በቀር በሽማግሌ ላይ የሚቀርብ ክስ አትቀበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ካልመሰከሩበት በቀር በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ላይ የሚቀርበውን ክስ አትቀበል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሁለት ወይም ከሦስት ምስክር በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሁለት ወይም ከሦስት ምስክር በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል። |
እኔም ‘ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ፥ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም፤’ ብዬ መለስሁላቸው።
“በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ፥ አንድ ምስክር አይበቃም፤ ጉዳዩ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት መረጋገጥ አለበት።