ጌታ እንዲህ ይላል፤ የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፤ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፤ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።
1 ጢሞቴዎስ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጣት መበለታትን ግን በመዝገብ ላይ አታካትት፤ ሥጋዊ ምኞታቸው ከክርስቶስ ስለሚለያቸው መጋባትን ይፈልጋሉና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወጣት መበለቶችን ግን እንዲህ ባለው መዝገብ አትጻፋቸው፤ ምክንያቱም ሥጋዊ ፍላጎታቸው ለክርስቶስ በገቡት ቃል ላይ በሚያይልበት ጊዜ ለማግባት ይሻሉና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሎቻቸው የሞቱባቸው በዕድሜ ያልገፉ ሴቶች ሥጋዊ ምኞታቸው አሸንፎአቸው ለክርስቶስ ያላቸው ፍቅር ሲቀነስ ባል ማግባት ስለሚፈልጉ እነርሱን በመበለቶች መዝገብ አትጻፋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባል የሞተባቸውን ቆነጃጅት ግን አትቀበል፤ በክርስቶስ ላይ ተነሥተው ሲቀማጠሉ ሊያገቡ ይወዳሉና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባል የሞተባቸውን ቆነጃጅት ግን አትቀበል፤ በክርስቶስ ላይ ተነሥተው ሲቀማጠሉ ሊያገቡ ይወዳሉና፤ |
ጌታ እንዲህ ይላል፤ የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፤ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፤ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።
እንግዲህ ወጣት መበለታት እንዲያገቡ፥ ልጆችንም እንዲወልዱ፥ እያንዳንዳቸውም ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስተዳድሩ እፈቅዳለሁ፤ በዚህም ተቃዋሚ የሚሳደብበትን ምንም ዓይነት ሰበብ እንዳይሰጡት ነው፤
አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቁጣ ወይን ጠጅ ጠጥተዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርሷ ጋር ሴስነዋልና፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሣ ሀብታሞች ሆነዋልና፤” ብሎ ጮኸ።
ራስዋን በአከበረችበትና በተቀማጠለችበት ልክ ሥቃይንና ኀዘንን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ መበለትም አልሆንም፤ ኀዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥