ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
1 ሳሙኤል 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌዋውያኑም የጌታን ታቦትና የወርቅ ዕቃዎቹን የያዘውን ሣጥን አውርደው በትልቁ ቋጥኝ ላይ አኖሩ። በዚያችም ዕለት የቤትሼሜሽ ሕዝብ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ መሥዋዕቶችንም ሠዉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋውያኑም የእግዚአብሔርን ታቦት፣ የወርቅ ዕቃዎቹን ከያዘው ሣጥን ጋራ አውርደው በትልቁ ድንጋይ ላይ አኖሩ። በዚያችም ዕለት የቤትሳሚስ ሕዝብ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ መሥዋዕቶችንም ሠዉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ታቦትና ከእርሱ ጋር የነበረውን ወርቅ የሞላበት ሣጥን አንሥተው በታላቁ ቋጥኝ ላይ አስቀመጡ፤ የቤትሼሜሽም ሰዎች የሚቃጠልና ሌላውንም መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት፥ ከእርስዋም ጋር የነበረውን የወርቅ ዕቃ ያለበትን ሣጥን አወረዱ፤ በታላቁም ድንጋይ ላይ አኖሩት፤ በዚያም ቀን የቤትሳሚስ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቍርባን አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት፥ ከእርሱ ጋር የነበረውንም የወርቅ ዕቃ ያለበትን ሣጥን አወረዱ፥ በታላቁም ድንጋይ ላይ አኖሩት፥ በዚያም ቀን የቤትሳሚስ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ መሥዋዕትንም ሠዉ። |
ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
ሕዝቡንም እንዲህ ብለው አዘዙ፦ “የአምላካችሁን የጌታን ቃል ኪዳን ታቦቱንና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ እርሱን በመከተል፥
የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፥ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሼሜሻዊው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የጌታን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ምስክር ነው።