La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 2:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በሰዎች ሰይፍ ያልቃሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከመሠዊያዬ የማላስወግዳቸው ዘሮችህ በሕይወት የሚተርፉትም ዐይኖችህን በእንባ ለማፍዘዝ፣ ልብህን በሐዘን ለማደንዘዝ ብቻ ነው፣ ሌሎቹ ዘሮችህ ግን በሙሉ በለጋነታቸው በዐጭር ይቀጫሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በወጣትነት ዕድሜአቸው በሰይፍ ያልቃሉ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዐ​ይ​ኖቹ የሚ​ፈ​ጽም በነ​ፍ​ሱም የሚ​ተጋ ሰውን ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አላ​ጠ​ፋም። ከቤ​ትህ የሚ​ቀ​ሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጐ​ል​ማ​ሶች ሰይፍ ይሞ​ታሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከመሠዊያዬ ያልተቆረጠ ልጅህ ቢገኝ ዓይንህን ያፈዝዘዋል፥ ነፍስህንም ያሳዝናል ከቤትህም የሚወለዱ ሰዎች ሁሉ በጎልማስነት ይሞታሉ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 2:33
9 Referencias Cruzadas  

እርሱም ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፥ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ ካህኑንም አብያታርን፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን ጠርቶአል፥ ባርያህን ስሎሞንን ግን አልጠራውም።


ስለዚህ ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር አሴረ፤ እነርሱም አዶንያስን ደገፉት።


እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሃትን፥ ነፍስን የሚያኮስስና ዓይንን የሚያፈዝዝ ክሳትና ትኩሳት አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ይበሉታልና ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።


እነሆ በእስራኤል በረከት ሁሉ በማደሪያዬ ጠላትህን ታያለህ፤ በቤትህም ለዘለዓለም ሽማግሌ አይገኝም።


ይህ በሁለቱ ልጆችህ በሖፍኒና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።


ንጉሡም ኤዶማዊውን ዶይቅን፥ “እንግዲያውስ አንተው ዞረህ ካህናቱን ግደላቸው” ብሎ አዘዘው። ኤዶማዊው ዶይቅም ዞረና ገደላቸው። በዚያች ዕለት ሰማንያ አምስት የበፍታ ኤፉድ የለበሱ ካህናትን ገደለ።