La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 18:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት ግን ሳኦልን፥ “የንጉሥ ዐማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ቤተሰቤም ሆነ የአባቴ ወገን በእስራኤል ዘንድ ምንድነው?” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት ግን ሳኦልን፣ “የንጉሥ ዐማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ቤተ ሰቤም ሆነ የአባቴ ጐሣስ በእስራኤል ዘንድ ምንድን ነው?” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊትም “የንጉሥ ዐማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ቤተሰቤስ በእስራኤል መካከል እምን ቊጥር ይገባል?” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰው​ነ​ቴስ ምን​ድን ናት? የአ​ባ​ቴስ ወገን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ምን​ድን ነው?” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ሳኦልን፦ ለንጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰውነቴስ ምንድር ናት? የአባቴስ ወገን በእስራኤል ዘንድ ምንድር ነው? አለው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 18:18
9 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባ፤ በጌታ ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከዚህ ያደረስኸኝ ኧረ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድንነው?


ከሰሎሞን ሴቶች ልጆች መካከል ባስማት ተብላ የምትጠራውን አግብቶ የነበረ አሒመዓጽ፦ የንፍታሌም ግዛት አስተዳዳሪ።


ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “ወደ ፈርዖን የምሄድና የእስራኤልንም ልጆች ከግብጽ የማወጣ እኔ ማን ነኝ?” አለው።


ጌታን መፍራት የጥበብ ትምህርት ነው፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።


ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።


እኔም፦ “ወዮ! ጌታ አምላኬ፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እንዴት እንደምናገር አላውቅም” አልሁ።


በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦ “እኔ ባዕድ ሆኜ ሳለሁ፥ ስለ እኔ ታስብ ዘንድ፥ እንዴት በፊትህ ሞገስ አገኘሁ?” አለችው።


እነርሱም ይህንኑ ለዳዊት ደግመው ነገሩት፤ ዳዊት ግን “ለመሆኑ የንጉሥ ዐማች መሆንን እስከዚህ ትንሽ ነገር አድርጋችሁ ትቆጥራላችሁን? እኔ አንድ ምስኪን ድኻና እውቅና የሌለኝ መሆኔን አጣችሁትን?” አላቸው።


ሳኦልም፥ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ውስጥ በጣም አነስተኛ ከሆነው ከብንያም ወገን አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? ታዲያ እንዲህ ያለውን ነገር ስለምን ትነግረኛለህ?” ብሎ መለሰለት።