La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 15:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕዝቡ ግን በጌልገላ ለአምላክህ ለጌታ ለመሠዋት ከምርኮው ከተለዩት መካከል፥ ምርጥ ምርጡን በግና በሬ ወስደዋል።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰራዊቱ ግን ከምርኮው ከተለዩት መካከል፣ ምርጥ ምርጡን በግና በሬ፣ በጌልገላ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ ወስደዋል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ወታደሮቼ የማረኩአቸውን ምርጥ ምርጥ የሆኑ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን አልገደሉአቸውም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በጌልገላ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ አምጥተዋቸዋል።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝቡ ግን ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጌ​ል​ጌላ ይሠዉ ዘንድ ከእ​ርሙ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ከም​ር​ኮው ወሰዱ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕዝቡ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችንና በሬዎችን ከምርኮው ወሰዱ አለው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 15:21
5 Referencias Cruzadas  

አዳምም፦ “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኽኝ ሴት እርሷ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” አለ።


ጌታ እግዚአብሔርም ሴቲቱን፦ “ይህ ያደረግሽው ምንድነው?” አላት። ሴቲቱም፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ” አለች።


ይህ በብዙ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና።”


ሳኦልም፥ “ሠራዊቱ ከአማሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጦቹ በጎችና በሬዎች ለጌታ ለአምላክህ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳይገድሉ የተዉአቸው ናቸው፤ የቀሩትን ግን በሙሉ አጥፍተናል” ብሎ መለሰ።