ባቂደስ ብዙ ወታደሮች ይዞ ከእነርሱ ጋር ሄደ፤ ዮናታንንና ጓደኞቹን እንዲይዙ በይሁዳ አገር ለሚገኙ የጦር ጓደኞቹ ሁሌ በሥውር ይጽፍላቸው ነበር። ግን ሐሳባቸው ከሸፈባቸውና ያሰቡት አልሆነላቸውም።