ባቂደስ ከኢየሩሳሌም ሄዶ ሰፈሩን በቤተዜት አደረገ፤ እርሷን ትተው ከሄዱትም ሰዎች መካከል ብዙዎችን አሠረ፤ እንዲሁም ከሕዝቡ አንዳንዶቹን አስያዘ፤ እንዲገደሉም አደረገ በኋላ በታላቁ ጉርጓድ ውስጥ ጣላቸው።