ነገር ግን በስተ ኋላ የነበሩት ሁሉ በሰይፍ ተመትተው ወደቁ። እስከ ጌዜሮንና እስከ ኤዶምያስ ሜዳ ድረስ፥ እስከ አዛጦንና እስከ ያምንያ ድረስ ተከታተሏቸው፤ ጠላት ሦስት ሺህ የሚያህሉ ሰዎች በዚያ አጣ።