ኢየሩሳሌም ባዶዋን ቀርታ ነበር፤ ከልጆችዋ ማንም የሚገባና የሚወጣ አልነበረም፤ ቤተ መቅደሱ ተበዝብዞ ነበር፤ አረመኔ ገብቶበታል፥ በያዕቆብ (በእስራኤል) እልልታዎች ተወግደዋል፤ ዋሽንትና ክራር አይሰሙበትም።