La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 8:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰሎሞን ጸሎቱን ከፈጸመ በኋላ እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ ከነበረበት መሠዊያ ፊት ተነሥቶ ቆመ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰሎሞንም ይህን ሁሉ ጸሎትና ልመና ለእግዚአብሔር አቅርቦ ከፈጸመ በኋላ፣ እጆቹን ወደ ሰማይ በመዘርጋት፣ በጕልበቱ ተንበርክኮ ከነበረበት ከእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ተነሣ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰሎሞን ጸሎቱን ከፈጸመ በኋላ እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ ከነበረበት መሠዊያ ፊት ተነሥቶ ቆመ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰሎ​ሞ​ንም ይህ​ችን ጸሎ​ትና ልመና ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸልዮ በፈ​ጸመ ጊዜ፥ በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ር​ክኮ፥ እጁ​ንም ወደ ሰማይ ዘር​ግቶ ነበ​ርና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ከሰ​ገ​ደ​በት ተነሣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰሎሞንም ይህችን ጸሎትና ልመና ሁሉ ለእግዚአብሔር ጸልዮ በፈጸመ ጊዜ፥ በጕልበቱ ተንበርክኮ እጁንም ወደ ሰማይ ዘርግቶ ነበርና ከእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ተነሣ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 8:54
9 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ሰሎሞን የእስራኤል ሕዝብ ሁሉም በተገኙበት ተነሥቶ በጌታ መሠዊያ ፊት ለፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘረጋ።


ሰሎሞንም ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላውን መሥዋዕት በላ፤ የጌታም ክብር ቤቱን ሞላ።


ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፥ በፈጠረን በእርሱ በጌታ ፊት እንበርከክ፥


እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንዲሁ መጸለይን አስተምረን፤” አለው።


ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፤ ተንበርክኮም፦


ከጸሎትም ተነሥቶ ወደ ደቀመዛሙርቱ መጣና ከኀዘን የተነሣ ተኝተው ሲያገኛቸው


ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ።


ጊዜውንም በፈጸምን ጊዜ ወጥተን ሄድን፤ ሁላቸውም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን፤